1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ንጹሕ ምንጭ ኢትዮጵያ የእደ ጥበባት ዓውደ ርዕይ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 10 2016

የዓዉደ ርእዩ መጠርያ ንጹሕ ምንጭ ኢትዮጵያ ይሰኛል። ኢትዮጵያ ብዙ ንጹሕ ምንጮች አልዋት። ከነዚህ ንጹሕ ምንጮች መካከል፤ የራስዋን ድርሳናት፤ ሥነ- ነገር የከተበችባቸዉ ፊደላት የሚጠቀሱ ናቸዉ። እግዚቢሽኑን የሚመሰገን ፤ የወጣቶቹ ሥራ ለሃገሪዉ ሃገሩን፤ ነባር ባህሉን እና እዉቀቱን እንዲያዉቅ የሚያደርግ ብዙ ምንጮችንም የሚያሳይ ነዉ።

https://p.dw.com/p/4ewUr
ንጹሕ ምንጭ  የብራና አዘገጃጀት፣ የእደ ጥበባት ዓውደ ርዕይ
ንጹሕ ምንጭ የብራና አዘገጃጀት፣ የእደ ጥበባት ዓውደ ርዕይ ምስል Solomon Muchie/DW

ንጹሕ ምንጭ ኢትዮጵያ የእደ ጥበባት ዓውደ ርዕይ

የዓዉደ ርእዩ መጠርያ ንጹሕ ምንጭ ኢትዮጵያ ይሰኛል። ኢትዮጵያ ብዙ ንጹሕ ምንጮች አልዋት። ኢትዮጵያ ካልዋት ንጹሕ ምንጮች መካከል፤ የራስዋን ድርሳናት፤ ሥነ- ነገር የከተበችባቸዉ  ፊደላት አሏት። ሥነ- ፊደል የምንለዉ የፊደላቱ አጣጣል፤ ሥነ ቅርጻቸዉ፤ የነበራቸዉ፤ የፊደል ቅርጽ ከሳባዉያን ዘመን ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ እንዴት ፊደሎቻችን ቀጠሉ፤ ፊደላችን ከየት መጣ የሚለዉ ሁሉን ነዉ። »  

ሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ ድርጅት ባለፈዉ እሁድ ታሪካዊ ያለዉን ዓዉደ  ርእይ እንዲህ በመሃል በአዲስ አበባ  ግዮን ሆቴል ቅጽር ጊቢ በደማቅ ሥነ-ስርዓት ለተመልካች ይፋ አድርጓል። ንጹሕ ምንጭ ኢትዮጵያ የተሰኘዉ እና እስከ ፊታችን እሁድ ሚያዝያ 13 ቀን ድረስ በሚዘልቀዉ በዚህ ዓዉደ ርእይ መክፈቻዉ ሥነ-ስርዓት ላይ የሃይማኖት አባቶች ተጋባዥ እንግዶች ነበሩ። በጊዮን ሆቴል ቅጽር ግቢ የተዘረጋዉ ንጹሕ ምንጭ የተሰኘዉ ዉደ ርእይ የኢትዮጵያን ጥንታዊ የሥነ-ጥበብ ፤ ጥንታዊ አሳሳል ብልሃት፤ እደ-ጥበብ ፤ የመጽሐፍ ዝግጅት፤ ኪነ-ጽሕፈት ላይ ያተኮረ እንደሆን የዓዉደ ርእዩ አዘጋጅ የሐመረ ብርሃን የብራና መጽሐፍት ድርጅት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ኪሩቤል ታምራት ተናግረዋል።

ንጹሕ ምንጭ  የብራና አዘገጃጀት፣ የእደ ጥበባት ዓውደ ርዕይ
ንጹሕ ምንጭ የብራና አዘገጃጀት፣ የእደ ጥበባት ዓውደ ርዕይ ምስል Hamere Berhan Institute

«ዓዉደ ርእዩ ይህን የሚያሳይ ነዉ። እያንዳንዱ ከኢትዮጵያ መንጭተዉ ዓለምን ያረኩ ተግባሮች የሚያሳይ ነዉ። ሥራቸዉን አጀማመራቸዉን፤ ታሪካቸዉን፤ ተናግሮ ትግበራቸዉን ማንኛዉም ሰዉ እየዳሰሰ እየሰራ ሊተገብራቸዉ ታስቦ የተዘጋጀ አዉደ ርዕይ ነዉ። እንደሚታወቀዉ መጀመርያ ፊደላት መነሻዎቻችን ናቸዉ። ንጹሕ ምንጭ ካስባሉን አንደኛዉ ፊደላችን ነዉ። ከፊደሎች መነሻ አንጻር ታሪክ በደንብ የሚዳስስ እና ደሞ ፊደሉ ብራና ላይ ሲጻፍ እያንዳንዱ ሂደቱን የሚያሳይ ነዉ። የመጀመርያዉ ትዕይንት የቀለም ዝግጅቱን፤ የቆዳ የብራና አዘገጃጀቱን፤ ያሳያል። በመቀጠል የሚመጣዉ ሥነ-ስዕላችን ነዉ። ሥነ-ስዕሎቻችን እንዴት  እንዳደገ ፤ እንዴት እዚህ እንደደረሰ፤ ወርቃማ የስዕል ጊዜ የሚባለዉ የቱ ነዉ? መቼ ነዉ? እነዚህን ሁሉ ነገሮች ዓዉደ ርእዩ ያሳያል። ከዝያ በኋላ ደግሞ አሁን በተለይ ደግሞ ሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ ድርጅት እየሰራቸዉ ያሉ፤ በተለይ ደግሞ ስልጠና እየሰጠ መሆኑን የሚያሳየዉ ነዉ። ለኢትዮጵያዊ ስዕል ልኬት ሰጥቶ ከ ሰባት ዓመት እስከ አስራ አራት ዓመት ክልል ላሉ ልጆች ፤ ከዝያ በላይም ላሉ ወጣቶች በአዳር ይዞ የሚሰጠዉን ስልጠና ነዉ። ትልልቆችን ያማከሉ የስዕል ሥልጠና መዓቀፉችን የሚያሳይ ነዉ። የተግባረድ ማሳያዉ የአንጥረኛ ስራዉንም፤ ሰሙን ቅርፅ እያወጡ ማዕድናቱን እያቀለጡ ነሃሱን ንኬሉን መዳቡን እያቀለጡ የሚያሳዩበት፤  እዛዉ ከነሙሉ  የስራ ሂደቱ የሚታይበት ነዉ።  ሌላዉ የእንጨት ፍልፍሉ ሥራ፤ የሸክላ ሥራ፤ የሽመና ሥራ፤ ከጥጥ መፍተል ጀምሮ እያንዳንዱን ነገር በሚያሳይ መንገድ የተቀረፀ እና የቀረበ ፤ የተግባረድ ማሳያዉ። »    

ንጹሕ ምንጭ  የብራና አዘገጃጀት፣ የእደ ጥበባት ዓውደ ርዕይ
ንጹሕ ምንጭ የብራና አዘገጃጀት፣ የእደ ጥበባት ዓውደ ርዕይ ምስል Hamere Berhan Institute

ሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ ድርጅት፤ በዋናነት እንደስሙ መነሻ አድርጎ የተነሳዉ የብራና መጽሐፍትን ቢሆንም፤ ተቋሙ የተለያዩ ጥንታዊ የሚባሉ የተግባረድ ሥራዎችን የሚሰራ፤ ይህንኑ ሥራ የሚያሰለጥን ተቋም እንደሆነ እና በሥሩ ወደ 62 ሠራተኞች እና ወደ 120 የሚሆኑ አገልጋዮች ያሉት ተቋም እንደሆነ አቶ ኪሩቤል ተናግረዋል።  የብራና መጻሕፍት ጥንታዊነት ታሪካዊነት ከስድስተኛዉ መቶ ክፍለዘመን ጀምሮ ያለ ታሪክ በዓዉደ ርእዩ ላይ እንደሚጠቀስ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊዉ አቶ ኪሩቤል ታምራት ገልፀዋል።  

ንጹሕ ምንጭ  የብራና አዘገጃጀት፣ የእደ ጥበባት ዓውደ ርዕይ
ንጹሕ ምንጭ የብራና አዘገጃጀት፣ የእደ ጥበባት ዓውደ ርዕይ ምስል Hamere Berhan Institute

« ከቀደመ ታሪክ ጀምሮ ፤ በተለይ በተጻፈ ታሪክ ላይ ተመርኩዞ በወንጌል ደረጃ ፤ ትልቁ እና እድሜ ጠገቡ የሚባለዉ፤  የአባ ገሪማ እስካሁን በስድስተኛዉ ክፍለዘመን ተጽፎ 1600/ 1500 ዓመት የሆነዉን ቅዱስ ወንጌልን፤ መነሻ አድርገን ከፊደላት ከታች፤ ጀምሮ ማለትም ከሳባዉያን ፊደላት ጀምሮ ፤ እስካሁን ድረስ በነ አባ ሰላማ እንዴት እንዳደገ ፊደላቱን በሚያሳይ ሁኔታ የቀረበ ነዉ።  ታሪኩንም ከመናገር ጀምሮ ከነትግበራዉ ፊደላቶቹም እዛዉ የተጻፉ የሚሰሩ የሚታዩበት ነዉ።    

አቶ ኪሩቤል ታሪካዊዉ፤ ንጹሕ ምንጭ ኢትዮጵያ ዓዉደ ርእይ ምን አላማ ይዞ ይሆን ይህን በአይነቱ ለየት ያለ እና የጥንታዊ አሳሳል ብልሃት፤ እደ-ጥበብ ፤ የመጽሐፍ ዝግጅት ፤ ኪነ-ጽሕፈት ላይ ያተኮረ ኤግዚቢሽንን የከፈተዉ?ለሚለዉ ጥያቄ የሚከተለዉን መልስ ሰጥተዋል።

ንጹሕ ምንጭ  የብራና አዘገጃጀት፣ የእደ ጥበባት ዓውደ ርዕይ
ንጹሕ ምንጭ የብራና አዘገጃጀት፣ የእደ ጥበባት ዓውደ ርዕይ ምስል Hamere Berhan Institute

« ይሄንን በተለይም ኢትዮጵያዉያን በእጅ ስራችን የታወቅን ብዙ በቀደምት ምንጭነታችን እንታወቅ ነበር፤ በኋላም በጊዜ ሂደት ዉስጥ ብዙ እየተሰሩብን ያሉ፤ በተለይ ተግባረድ ስራዎች እንዲጠሉ እንዲነቀፉ፤ ሌላ ስም እንዲሰጣቸዉ ብዙ ጥረት ተደርጓል። እነዚህ  ባለሞያዎች በጣም እንዲቋሸሹ ገለል እንዲደረጉ ተደርጓል። ይህንን ታሪክ ለማድረግ ፤ ወጣቶች፤ በማኅበረሰብ ዉስጥ ተቀባይነት ያላቸዉ ሰዎች እንዲሰሩት እንዲተገብሩት ፤ ማድረግ እንዲቻል፤ ይህንንም ስል የበለጠ የሚያስመሰግን፤ የበለጠ የሚያኮራ ስራ  እንደሆነ ለትዉልዱ እንዲያሳይ፤ የአባቶቻችን የእዉቀት ጥበብ ይህ እንደነበር፤ መልክት የሚያስተላልፍ የሚያሳይ ዓዉደ ርዕይ እንዲሆን ነዉ የታቀደዉ በዚህም መልኩ ለህዝብ ይፋ ተደርጓል። ከዚህ ሌላ ተቋሙ ካለበት የቦታ አንጻር፤ ማኅበረሰቡ የራሱን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ፤ ለማሳሰብም ጭምር ነዉ። በጣም ሰፊ bpota የሚወስድ ስራ ነዉ። አሁን እየሰራንበት ያለዉ ቦታ ፒያሳ አካባቢ አሮጌዉ ፖስታ ቤት ቅጽር ጊቢ ዉስጥ ነዉ። በአሁኑ ጊዜ ፒያሳ ካለበት የልማት እንቅስቃሴ አንጻር ቦታዉ ተፈላጊ በመሆኑ ፤ እዛዉም ቢሆን ቦታዉ በጣም ጠባብ እና ለመስራት አመቺ ባለመሆኑ  ሰዎች ይህን ተረድተዉ ሰፊ ቦታ እንድናገኝ የሚመለከታቸዉ አካላት ችግራችንን ተረድተዉ ሰፊ ቦታ እንዲሰጡን ለመጠየቅም ጭምር ነዉ። »   

ንጹሕ ምንጭ  የብራና አዘገጃጀት፣ የእደ ጥበባት ዓውደ ርዕይ
ንጹሕ ምንጭ የብራና አዘገጃጀት፣ የእደ ጥበባት ዓውደ ርዕይ ምስል Hamere Berhan Institute

በአዲስ አበባ ጊዮን ሆቴል ቅጽር ግቢ የተዘረጋዉን ዓዉደ ርእይ የጎበኙ እና በወጣቶቹ የእደ- ጥበብ ሥራ የተደነቁት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአለ የሥነ-ጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት ዳይሬክተር አቶ አገኘሁ አዳነ እግዚቢሽኑን የሚመሰገን ብለዉታል።  የወጣቶቹ ሥራ ለሃገሪዉ ሃገሩን ፤ ነባር ባህሉን እና እዉቀቱን እንዲያዉቅ የሚያደርግ መሆኑንም ተናግረዋል።  

«  ሐመረ ብርሃን የብራን የተsbal,ዉ የወጣቶች ስብስብ  ጥንታዊ ከአብነት ትምህርት ቤቶች ፤ ከጥንታዊት ቤተ ክርስትያን፤ የተገኘዉን የኪነ-ጽሕፈት፤ የብራና ዝግጅት፤ የብራና ስዕሎች፤ የብራና መጻሕፍት፤ የእደ ጥበብ ማለትም ብረት ማቅለጥን ጨምሮ፤ ይሰሩ የነበሩ ጥንታዊ የእደ ጥበብ ዉጤቶችን የተመለከተ፤ ትልቅ እግዚቢሽን ነዉ፤የሚመሰገን ኤግዚብሽን ነዉ።   

ሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ ድርጅት ተማሪዎች እና ሰራተኞች ጥንታዊዉን የእደ-ጥበብ፤ የኪነ-ሥልዕ እና ሥነ-ፅሑፍን አጥንተዉ ፤ በዘመኑ ትዉልዱ እንዲሰራዉ በማድረግ ማስቀጠላቸዉ ዘመኑ ትርፍ የሚያገኝ ይሆናል ሲሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አለ የሥነ-ጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት ዳይሬክተር አቶ አገኘሁ አዳነ አክለዋል።

ንጹሕ ምንጭ  የብራና አዘገጃጀት፣ የእደ ጥበባት ዓውደ ርዕይ
ንጹሕ ምንጭ የብራና አዘገጃጀት፣ የእደ ጥበባት ዓውደ ርዕይ ምስል Hamere Berhan Institute

በመክፈቻዉ ሥነ-ስርዓት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስትያን፤ የጠቅላይ ቤተ-ክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ  እና የባህርዳር አገረ ስብከት ሊቀ-ጳጳስ አቡነ አብርሃም፤ ስለ ዓዉደ ርእዩ ያልሰሙ የቤተ-ክርስትያኒቱ ምዕመናን እግዚቢሽኑን እንዲጎበኙ ጥሪ አስተላልፈዋል።

የሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ ድርጅት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ኪሩቤል ታምራት እንዲሁም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አለ የሥነ-ጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት ዳይሬክተር አቶ አገኘሁ አዳነ ለሰጡን ቃለ ምልልስ በዶቼ ቬለ ስም እያመሰገንን እያመሰገንን ሙሉ ዝግጅቱን የድምጽ ማድመጫ ማዕቀፉን በመቻን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።

 

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ