1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዩክሬን የአውሮጳ ኅብረት አባል ለመሆን ማመልከቷ

ረቡዕ፣ የካቲት 23 2014

የዩክሬን ሩሲያ ጦርነት ሰባተኛ ቀኑን በያዘበት በዛሬው ቀንም ቀጥሏል። የዩክሬን ፕሬዚደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ሀገራቸው የአውሮጳ ኅብረት አባል እንድትሆን በጠየቁበት ማግስት ዛሬ ኅብረቱ ለሀገራቸው ትብብር እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

https://p.dw.com/p/47uDz
Russland Langstrecken-Marschflugkörper
ምስል Russian Defense Ministry Press Service/AP Photo/picture alliance

ሒደቱ የሚወሰነው በኅብረቱ ስብሰባ ነው

የዩክሬን ሩሲያ ጦርነት ሰባተኛ ቀኑን በያዘበት በዛሬው ቀንም ቀጥሏል። የዩክሬን ፕሬዚደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ሀገራቸው የአውሮጳ ኅብረት አባል እንድትሆን በጠየቁበት ማግስት ዛሬ ኅብረቱ ለሀገራቸው ትብብር እንዲያደርግ ጠይቀዋል። «ከእኛ ጋር ስለመሆናችሁ አረጋግጡልን» ሲሉም በንግግራቸው ተሰምተዋል። ፕሬዚደንቱ የአውሮጳ ኅብረት ወታደራዊ ትብብር እንዲያደርግላቸው መጠየቅ የጀመሩት ቀደም ሲል ነበር። የሩስያ ጦር ወደ ዩክሬን ዘልቆ በገባ በ48ኛው ሰአት ቅዳሜ ዕለት ብራስልስ ደውለው የአውሮፓ ኅብረት ወታደራዊ ትብብር ጠይቀው ነበር። ወታደራዊ ትብብሩ ቀጥተና ምላሽ ባያገኝም የአውሮጳ ኅብረት ውስጥ ዩክሬን እንድትቀላቀል ያቀረቡት ጥያቄ ግን ተቀባይነት አግንቷል። ሒደቱ የሚወሰነው በኅብረቱ ስብሰባ ሲሆን የሚሳካ እንኳን ቢሆን ዓመታት ሊወስድ እንደሚችል የብራስልሱ ወኪላችን ገበያው ንጉሤ የላከልን ዘገባ ይጠቁማል። 

ሰባተኛ ቀኑን የያዘው የዩክሬን ሩሲያ ጦርነት ዛሬም ቀጥሎ ውሏል። ከሶስት አቅጣጫ የተሰነዘረው የሩሲይ ጥቃት ዋና ከተመዋን ኪየቭን ለመክበብ የተቃረበ መሆኑ እየትገለጸ ነው። እስካሁን ከ400 በላይ ሲቪሎች የተገደሉ መሆኑን የዩክሬን ባለስልጣኖች የገለጹ ሲሆን፤ ከ600 ሺ በላይ ሰዎች ደግሞ ወደ ጎርቤት የአውሮፓ አገሮች እንደገቡ ታውቋል። 

ፕሬዝዳንት ፑቲን ባለፈው ሀሙስ  ዩክሬንን ከወታደራዊ ቀጣናነት ነጻ ለማደረግና  በሳቸው አገላለጽ ለዩክሬንም ሩሲያም ስጋት የሆኑትን የኪዬቭ  አፍቃሪ ናዚ መሪዎችን ለማስወገድ ልዩ ተለእኮ ያለውን ጦራቸውን ወደ ዩክሬን ማዝመታቸውን ማስታወቃቸው ይታወሳል። ይህን የሞስኮን ውሳኔ የአውሮፓ ህብረትና ኔቶ አባል አገሮች መቃወም ብቻ ሳይሆን  ከወታደራዊ ግብ ግብ ውጭ ያሉትን አማራጮች ሁሉ በመጠቀም ከሩሲያ ባንኮችና ኩባንያዎች ጋር ምንም አይነት ንግድ እንዳይደረግና የገንዘብ ልውውጥ እንዳይኖር የሚያስችሉ ውሳኔዎች አስተላልፈዋል። ፕሬዝዳንት ፑቲንን ጨምሮ በፓርላማ አባላት፣ የመንግስትና የጦር ባለስልጣኖች ላይ ማዕቀብ ጥለዋል ። የሩሲያ አውሮፕላኖች በአውርፓና በአሜርካ፤ ካናዳ ብርታኒያና አውስትራሊያ ጭምር  እንዳይበሩና እንዳያርፉም ከልክለዋል። በአንጻሩ ለዩክሬን ማንኛውንም አይነት የጦር መሳሪያና የገንዘብ እርዳታ በማድረግ የዩክርኖችን ጸረ ሩሲያ ትግል በከፍተኛ ሁኒታ  እየደገፉ ይገኛሉ።ይህ በሩሲያ አንጻር የአውርፓ ህብረትና የምእራቡ አለም ባጠቃላይ የፈጠሩት አንድነትና ጥምረት ከተጠበቀው በላይ ሆኖ ታይቷል። 

Deutschland | Ankunft ukrainischer Flüchtlinge in Berlin
ምስል Hannibal Hanschke/Getty Images

ዩክሬናውያንና ፕሬዝዳንታቸው ሚስተር ዜሌንስኪ፣ ጦርነቱ የከፋ መሆኑን በመግለጽ አውርፓውያን አሁን እያደረጉት ካለው በላይ ደጋፋቸውን እንዲያደርጉ ብቻ ሳይሆን ዩክሬን የህብረቱ አባል እንድትሆን፤ የዩክክሬን ሰማይም ከማንኛውም አይነት በረራ ነጻ እንዲደረግ እየጠየቁ ነው፡ ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪ ትናንት በቪዲዮ ለአውሮፓ ፓርላማ ባደረጉት ንግግር፤ ጥንካሬያችንና ቁርጠኘነታችንን እያሳየን ነው። በዚህ ወቅት እናንተም ከኛ ጋር መሆናችሁን በተግባር እንድታረጋግጡልን እንፈልጋለን በማለት የአገራቸውን የአባልነት ጥያቄ ፓርላማው እንዲደግፈው ጠይቀዋል። የፕሬዝዳንት ዜሌንስኪን ንግግር በሞቀ ጭብጨባ ያጀበው የአውሮፓ ፓርላማ፤  ሩሲያ ጦርነቱን እንድታቆም፣ ለዩክሬን የሰባዊ እርዳታ እንዲደረግና ህብረቱ ዩክሬንን በእጩ አባልነት እንዲቀበላት ውሳኔ አስተላለፏል ። ይሁን እንጂ የአውሮፓ ህብረት አባልነት የሚወሰነው በመሪዎቹ ስብሰባ ሲሆን፤ ጥያቄው ተቀባይነት ማግኘቱን ብዙዎች ይጠራጠራሉ። በልዩ ሁኒታ እጩ አባል ብትሆንም እንኳ፤ አባል ለመሆን በርካታ ቅድመሁታዎችን ማሟላት ያለባት በመሆኑ ሂደቱ  አመታትን ሊወስድ እንደሚችል  ነው የህብረቱን አሰራር የሚያውቁት ባለሙያዎች የሚናገሩት ።  
የዩክሬንን ሰማይ ከማናቸውም በረራ ነጻ የማደረጉን ወይም የኖ ፍላይ ዞን ጥያቄን በሚመለክትም  የኔቶም ሆኑ የህብረቱ አገሮች ሊተገብሩት እንደማይችሉ ወይም እንደማይፈልጉ በግልጽ አስታውቀዋል። የብራታኒያው ጠቅላይ ሚኒስተር ቦሪስ ጆንሰን የኖ ፍላይ ዞንን ውሳኔ አንደምታ  ሲያስረዱ፤ ይህ ማለት ብርታኒያ በሩሲያ አውሮፓላኖች ላይ መተኮስ ማለትና  በቀጥታ ጦረነቱ ውስጥ መግባት ማለት ነው በማለት ይህ  የሚደረግ እንዳልሆነ ገልጸዋል። 

Deutschland | Ankunft ukrainischer Flüchtlinge in Berlin
ምስል Hannibal Hanschke/Getty Images

ከዚያ በመለስ ግን ለዩክሬን የማይደረግ ደጋፍ፤ በሩሲያ ላይ የማይወሰን ተጽኖ ፈጣሪ ውሳኔ እንደማይኖር ነው የኔቶም የህበረቱም መሪዎችና ባልስልጣኖች እየተናገሩ ያሉት። የአውሮፓ  ኮሚሺን ፕሬዝድናት ወይዘሮ ኡርሱላ ቮንዴርልየን  ትናንት በአውሮፓ ፓርላማ ባሰሙት ንግግርም፤ ህብረቱ ከዚህ በፊት ተደርጎ በማይታወቅ ሁኒታ  ከህብረቱ በጀት በ500 ሚሊዮን ኢሮ መሳሪያ ተገዝቶ ለዩክሬን እንዲሰጥና ሌላ 500 ሚሊዮን ኢሮ ደግሞ ለሰባዊ  ድጋፍ እንዲሰጥ  የወሰነ መሆኑን አስታውቀዋል። የአውሮፓ ህብረትም ሆነ የኔቶ አባል ገአሮች የዩክሬን ድጋፍ በሁሉም ዘርፍ ተጠናክሮ የቀጠለ ቢሆንም፤ ይህ ሁሉ ግን ጦርነቱን በአጭር ግዜ የሚያቆመው መሆኑን የሚጠራጠሩ ጥቂቶች አይድለም። ሩሲያ ወደዚህ ጦረንት የገባቸው በዋናነት ኔቶ በምስራቅ አውሮፓ በሚያደርገው መስፋፋትና በተለይም ዩክሬንን አባል በማድረግ ለደህንነቷ ስጋት የፈጠረባት በመሆኑ እንደሆነ ስትገልጽ ቆይታለች። 

ገበያው ንግሴ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ
እሸቴ በቀለ