1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ኅብረት ልዩ የመሪዎች ጉባኤ አጀንዳዎችና ውሳኔዎች

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 10 2016

ረቡዕ ሚያዝያ 9 ቀን የጀመረው የ27ቱ የአውሮጳ ኅብረት አገሮች የመሪዎች ስብሰባ ዛሬ ከስአት በኋላ ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቅቋል ። የጉባኤው አጀንዳ ምን ነበር? ትናንት እና ዛሬ የተከናወነው የኅብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ምንስ ውሳኔ አሳልፎ ተጠናቀቀ?

https://p.dw.com/p/4ewD2
27ቱ የአውሮጳ ኅብረት አገሮች የመሪዎች ስብሰባ
27ቱ የአውሮጳ ኅብረት አገሮች የመሪዎች ስብሰባምስል Kenzo Tribouillard/AFP/Getty Images

የኅብረቱ ጉባኤ ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል

ረቡዕ ሚያዝያ 9 ቀን፣ የጀመረው የ27ቱ የአውሮጳ ኅብረት አገሮች የመሪዎች ስብሰባ ዛሬ ከስአት በኋላ ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቅቋል ።  የጉባኤው አጀንዳ ምን ነበር? ትናንት እና ዛሬ የተከናወነው የኅብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ምንስ ውሳኔ አሳልፎ ተጠናቀቀ? 

ከትናንት ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው የ27ቱ የአውሮጳ ህብረት  አገሮች የመሪዎች ስብሰባ ዛሬ ከስአት በኋላ ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል። ይህ ልዩ ስብሰባ በተለይ በህብረቱ የጋራ ገበያና ኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ እንዲያተኩር ታቅዶ የተጠራ ቢሆንም፤ የመካከለኛው ምስራቅ አጀንዳ በተለይ ኢራን በእስራኤል  ላይ የስነዘረችው ጥቃትና ሩሲያ በዩክሬን ላይ የክፈተችው ጦርነት ተጠናክሮ መቀጠሉ የመሪዎቹን የትኩረት አጀንዳ ሳያስለውጥ እንዳልቀረ ነው የሚገረው።

የህብረቱ ፕሬዝዳንትና የስብሰባው መሪ ሚስተር ቻርለስ ሚሸል በተለይ በነዚህ ማለት በዩክሬንና መካከለኛው ምስራቅ - ኢራን አጀንዳዎች ላይ የተላለፉትን ውሳኔዎች በጋዜጣዊ መግለጫቸው ግልጽ አድርገዋል። በቅድሚያ በዩክሬን ላይ የተላለፈውን ውሳኔ ሲያብራሩ  "አሁን የሚያስፈልገው ብዙ ውሳኔ ሳይሆን ብዙ ወታደራዊ መሳሪያ ነው። የአየር መካላከያ መሳሪያዎች እንደሚያስፈጉና ባስቸኳይ መላክ እንዳለባቸው መሪዎቹ አምነውበታል” በማለት  በተለይ አቅሙ ያላቸው አባል አገራት ይህንና ሌሎች የጦር መሳሪያዎችን ባስቸኳይ ሊልኩ እንደሚገባ የተስማሙ መሆኑን ገልጸዋል።

የዩክሬኑ መሪ ቅሬታና ጥያቄ

ዩክሬን፤ ከምራባውያኑ እየተገኘ ያለው የጦር መሳሪያና የገንዘብ እርዳታ በቂ ባለመሆኑ የሩሲያን ጦር መቋቋም ያቃታት መሆኑን በመግለጽ፤ አውሮፓ የሚስጠው ድጋፍ በአይነትና በብዛት እንዲጨምር እንዲሁም አሜሪካ ያቆየችውን የገንዘብ እርዳታ ትለቅ ዘንድ  እንዲያሸማግሉ የህብረቱን መሪዎች ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ቀድመው መጠየቃቸው ተገልጿል። በተለይ አሚሪካ ፈረንሳይና ብርታኒያ ኢስራኤልን ከኢራን ሚሳይሎች በመካላከል በኩል ያሳዩትን ተሳትፎ በመጥቀስ፤ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ለዩክሬን ለምን በተመሳሳይ ሁኒታ ድጋፍ አይደረግላትም በማለት  መጠየቃቸው ታውቋል፡፤  ለስብሰባው ባስተላለፉት መልክትም " የአውሮፓ አካል በሆነችው ዩክሬን  በመክከለኛው ምስራቅ ለምተገኘው እስራኤል ክቀናት በፊት የተደረገው አይነት መካላከል አይደረግላትም” በማለት የአየር መካላከያ መሳሪያ ከመስጠት አልፎ ለእስራኤል እንደተደረገው ወዳጆቿ ከሩሲያ ሚሳይሎች እንዲታደጓት አሳስበዋል።

ከ27ቱ የአውሮጳ ኅብረት አገሮች መሪዎች ስብሰባ ተካፋዮች በከፊል
ከ27ቱ የአውሮጳ ኅብረት አገሮች መሪዎች ስብሰባ ተካፋዮች በከፊል ። ከግራ ወደቀኝ፦ ሮቤርታ ሜትሶላ፤ ሻርል ሚሼል እና ኦላፍ ሾልትስምስል Omar Havana/AP/picture alliance

ለዩክሬን ጥያቄ የተሰጠው መልስ

የህብረቱ አባል አገራት በግልና ህብረቱ  ባጠቃላይ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ እንደጠየቁት ባይሆንም ሩሲያ እየፈጸመችው ካለው ጥቃት አንጻር ተጨማሪ ድጋፍ ማድረግ እንዳለባቸው ግን እንዳመኑበትና አንዳንዶች ለምሳሌ ጀርመን የአየር ማክላከያ መሳሪያ ለመስጠት መወሰኗ ታውቋል፡፤ ለምን እንደ እስራኤል  የህብረቱ አገሮች ዩክሬንን ከሩሲያ የሚሳይል ጥቃት በቀጥታ አይከላከሏትም ለሚለው ጥያቄ ግን መሪዎቹ አንድ አይነት መልስ ያላቸው አይመስሉም። የኔዘርላንድሱ ጠቅላይ ሚኒስተር ሚስተር ሩቶ ይህን በሚመለክት ምናልባትም እንዳብዛኞዎቹ የህብረቱ መሪዎች፤ ሁለቱን ማወዳደር ወይም ማቀላቀል ተገቢ አይደለም ነው የሚሉት፤ "ሁለቱን አናቀላቅላቸው ፡፤ እርግጥ ነው ዩክሬን የአየር መከላከያና ሌሎች መሳሪያዎችም ያስፈልጓታል” በማለት የፕሬዝዳንት ዘለንስኪን ስሜት እንደሚረዱ ግን ከመካከለኛው ምስራቅ ሁኔታ ጋር ማወዳደሩ ተገቢ እንዳልሆነ አስገንዝበዋል።

የመሪዎቹ ጉባኤ በመካከለኛ ምስራቅ ላይ

የመካከለኛው ምስራቅን በሚመለከት መሪዎቹ ያስተላለፉትን ውሳኔ ሚስተር ሚሸል ስገልጹ መጀመሪያ አሉ፤ " መጀመሪያ ኢራን በእስራኤል ላይ የፈጸመቸውን የሚሳይል ጥቃት አውግዘናል። በተለይ በድሮንና ሚሳይል  አምራች ኩብንያዎቿ ላይ ማዕቀብ ለመጣልም ተስማምተናል” በማለት ሁለቱም ወገኖች ግን ከተጨማሪ ግጭት ከሚያባብሱ እርምጃዎች እንዲቆጠቡ የህብረቱ መሪዎች ያሳሰቡ መሆኑን ገልጸዋል።  የህብረቱ መሪዎች በተጨማሪም አሁንም በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግና የእርዳታ አቅርቦት ያለምንም ችግር ለተቸገሩ እንዲደርስ እንዲደረግ ጥሪ አቅረበዋል።

የ27ቱ የአውሮጳ ኅብረት አገሮች የመሪዎች ስብሰባ ላይ ጆሴፍ ቦሬል በቪዲዮ ኮንፈረንስ ሲሳተፉ
የ27ቱ የአውሮጳ ኅብረት አገሮች የመሪዎች ስብሰባ ላይ ጆሴፍ ቦሬል በቪዲዮ ኮንፈረንስ ሲሳተፉምስል Lenoir/EUC/Ropi/picture alliance

ሊባኖስን ለመርዳት፤ ከቱርክ ጋር ለመስራት ከስምምነት ስለመደረሱ

የህብረቱ መሪዎች  የስራኤል-ሀማስ እንዲሁም የእስራኤል - ኢራን ግጭት፤ ወደ ሌሎች በተለይም ወደ ሊባኖስ እንዳይዛመት  ያላቸውቸውን ስጋት በመግለጽም ሊባኖችስን መርዳት የሚያስፈልግ ስለመሆኑ እንዳመኑበት ሚስተር ሚሸል አስታውቀዋል፡፤ በተጨማሪም የህብረቱንና ቱርክን ግንኙነት የበለጠ ለማሻሻል እንደሚሰሩና ለዚህም የቆፕሮስን ጉዳይ በመንግስታቱ ድርጅት የሰላም ማእቀፍ መፍታት እንደሚያስፈልግና ለዚህም ህብረቱ የበኩሉን ለማድረግ  መሪዎቹ የተስማሙ መሆኑ ታውቋል። የኔቶ የ75 ዓመት ጉዞና ፈተናዎቹ

የዚህ ወቅት የመሪዎቹ አጀንዳ በነበረው የጋራ  ገበያና ኢክኖሚ አጀንዳ ላይ በሁለተኛው ቀን ዉሎ  በተለይ በቀድሞው የጣሊያን ጠቅላይ ሚንስተር ሚስተር ኢንሪኮ ለታ በቀረበው ሪፖርት ላይ እንደተወያዩና የህብረቱን ፋይናንስ በማዋህድ ካፒታል ወደ ህብረቱ በሚፈስበት ወይም እዚሁ በህብረቱ በሚቆይበት ሁኔታ ላይ እንደመከሩም ተገልጿል ።

ገበያው ንጉሴ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ኂሩት መለሠ